“በተለያዩ ምርቶች እና ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ እና ምርት በደበቁ 66 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል” የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር

20

ባሕር ዳር: ነሐሴ 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ እንዳስታወቀው ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ጋር ተያይዞ ያላግባብ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ ከ1 ሺህ 200 በላይ ለሚኾኑ የተለያዩ ማኀበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ትምህርት ተሰጥጧል።
መምሪያው ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ እና ምርት እንዳይደበቅ ክትትል እያደረገ መኾኑንም አስታውቋል።

በዚህም በተለያዩ ምርቶች እና ሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ እና ምርት በደበቁ 66 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን መምሪያው አስታውቃል። በተመሳሳይ ተግባር ላይ ለነበሩ 89 ድርጅቶች ደግሞ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱም ተገልጿል።

የኑሮ ውድነትን እና የገበያ ዋጋ ለማረጋጋት በሚደረገው ጥረት ማኅበረሰቡ ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ እና ምርት በሚደብቁ አካላት ጥቆማ እንዲያደርጉ መምሪያው ጥሪ ማቅረቡን ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ አጠቃላይ የትምህርት ሥርዓቱ መፈተሽ እንዳለበት ተጠቆመ።
Next articleኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ክህሎት 88ኛ አባል ሀገር ኾና መመረጧን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።