“ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ የለበሰች ሀገር ለማስረከብ አሻራችንን እናኖራለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

23

ባሕር ዳር: ነሐሴ 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ክረምት ገፀ በረከት ነው፡፡ በክረምት ሁሉም ነገር የተፈጥሮን ውብ ዜማ ይከተላል፡፡ ምድሩ በአረንጓዴ ቀለም ይሞሸራል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እኛም በተፈጥሮ ዜማ እና በምድር መልክ ስልት ገጸ በረከት “ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ የለበሰች ሀገር ለማስረከብ አሻራችንን እናኖራለን” ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከስደተኞች ተመላሾች አገልግሎት የሥራ ኀላፊዎች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሂደናል ነው ያሉት፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት ሀገራችንን አረንጓዴ የማልበስ ዘመቻችንን በትጋት እንቀጥላለን ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ድብቁ የጤና እክል”
Next articleበተያዘው በጀት ዓመት የመንግሥት ገቢን ማሳደግ ላይ ዋነኛ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ አሕመድ ሺዴ ገለጹ።