
ባሕር ዳር: ነሐሴ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት “የፕሬዚዳንቱ የሕይዎት ዘመን ሽልማት” ተበርክቶለታል።
ሽልማቱ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለተሰጠ የላቀ አገልግሎት ዕውቅና የሚሰጥ ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላበረከተው ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ ይህ ሽልማት እንደተበረከተለት ከአየር መንገዱ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!