በዳባት ከተማ የሚገኙት የኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት አባላት የአቅመ ደካሞችን ቤት እየገነቡ ነው።

13

ባሕር ዳር: ነሐሴ 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቀጣናው የሚገኘው ክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ሸለመው ሙለታ ሠራዊቱ በአካባቢው ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ጉልበቱን ሳይሰስት ፈጥኖ ደራሽ መኾኑን ገልጸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤት ሠርተው ለአቅመ ዳካሞች እንደሚያስረክቡም ተናግረዋል።

መከላከያ ሠራዊቱ ለሀገር እና ለሕዝብ ዋስና ጠበቃ፣ ከደግነት እና ከቸርነት ቦታ የሚገኝ፣ ለቃሉ ታምኖ ለሙያው የሚገዛ እና ለተቸገሩ ወገኖች የበጎነት ሥራ ከማድረግ በተጨማሪ ለሀገር እና ለወገን ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ መኾኑንም አዛዡ አብራርተዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ከተማ የቀበሌ 03 ሊቀመንበር አበበ አሌ በበኩላቸው ክፍለጦሩ ለተቸገሩ ወገኖች ፈጥኖ በመድረስ መስዋዕትነት እየከፈለ ሰላም እና ደኅንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ እየጠበቀ እንደኾነ ገልጸዋል።

ከኢፌድሪ መከላከያ ሠራዊት ማኀበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በዳባት ከተማ የቀበሌ 03 ሊቀመንበር አበበ አሌ ክፍለ ጦሩ እያደረገ ላለው የበጎነት ተግባር ከፍተኛ አክብሮት እና ምስጋና አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየገበያ ጉድለት በመንግሥት አቅም ብቻ የማይሞላ በመኾኑ የግሉ ዘርፍ ሚና የጎላ መኾኑ ተገለጸ።
Next articleበዞኑ የኮሌራ በሽታ ሥርጭት እየጨመረ በመምጣቱ ኀብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የምዕራብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ አሳሰበ።