ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የሚዲያ ተቋማት የተሳተፉበት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ፡፡

18

አዲስ አበባ: ነሐሴ 2/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ በዘንድሮው 6ኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ!” በሚል መሪ መልዕክት በጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ የሚዲያ ተቋማት፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የኮሙዩኒኬሽን መሪዎች እና ሠራተኞች ተሳትፈው አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ከ2 ሺህ 500 በላይ ችግኝን የሚተክሉ ተሳታፊዎች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ እታለም መለሰ ተናግረዋል።

ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይኾን በየጊዜው መንከባከብ እና መጠበቅ እንደሚገባ አርቲስት ጥላሁን ጉግሳ ገልጸዋል።

ችግኝ ትከሉ ሲባል ብቻ ሳይኾን ሁሉም እራሱ በማሰብ ለሀገር የሚጠቅሙ ችግኞችን በመትከል ለትውልዱ አረንጓዴ ሀገር ማስረከብ እንዳለበትም ነው ያስገነዘቡት።

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዓመቱ የኢትዮጵያን ዕድገት ያስቀጠልንበት ኾኖ አልፏል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next articleበአማራ ክልል 350 ሺህ ሄክታር መሬት ቡናን ለመልማት የተመቼ መኾኑ ተገለጸ።