“ከ 7 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ወስደናል” የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር

20

ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ እና ምርት በመደበቅ ተግባር ላይ የተገኙ ከ7 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ አሥተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡

በውጪ ምንዛሪ አሥተዳደር ላይ የተደረገውን ለውጥ ምክንያት በማድረግ የተስተዋለውን የምርቶች ዋጋ መጨመር ለመግታት ከላይ እስከ ታች በተደራጀ አግባብ ክትትልና ቍጥጥር እየተደረገ መኾኑንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል። ሚኒስትሩ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሠራቱንም ነው የጠቀሱት፡፡

እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት መሠረታዊ ሸቀጦችን የጫኑ 1 ሺህ 649 ተሽከርካሪዎች ወደ ገበያ እየገቡ ነው። ከ115 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በስርጭት ሂደት ውስጥ ይገኛል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት የምርት እጥረት አለመኖሩን የገለጹት ዶክተር ካሳሁን ከሕገ ወጥ ተግባራቸው በማይቆጠቡ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማስገንዘባቸውን የኢፕድ ዘግቧል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱ ተገለጸ።
Next articleማሽን ለርኒንግ ምንድን ነው?