
ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 ደርሳል።
የኢትዮጵያ የደን ሽፋን የ#አረንጓዴዓሻራ ንቅናቄ ከተጀመረበት በ2011 ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደግ የቻለው ባላሰለሰ ጽኑ ጥረት ነው ብሏል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ባስተላለፈው መልእክት “በክረምቱ የችግኝ ሥራ መሪዎን ይከተሉ፤ አሻራዎን ይትከሉ” በሚል ጥሪ አቅርቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!