“ሰላማችንን፣ ፍቅር እና መቻቻላችንን ጠብቀን መኖር ትልቅ ጸጋ ነውና እንዳይለየን ጠብቁት” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

28

ደሴ: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ የሚታየውን ሰላም እና አብሮነት በዘላቂነት ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡ ለደሴ ከተማ ሁለንተናዊ ሰላም መረጋገጥ ሚና የነበራቸውን ሁሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመሥግነዋል፡፡

“ሰላማችንን፣ ፍቅር እና መቻቻላችንን ጠብቀን መኖር ትልቅ ጸጋ ነውና እንዳይለየን ጠብቁት” ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ይህን ያሉት የደሴ ዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት ነው፡፡

የደሴ እና አካባቢውን ማኅበረሰብ ከቱሪዝም መስክ ተጠቃሚ የሚያደርገው እና በሐይቅ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት በመልካም አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ መነቃቃት ከመፍጠር ባለፈ ስለፍቅር እና ብዝኀነት መማር እና ማወቅ ለሚፈልጉ ሁሉ መዳረሻ ይኾናል ነው ያሉት፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክቱ በታለመለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የአካባቢው ማኅበረሰብ ሰላሙን በማስጠበቅ የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ጀማል ይማም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የኮሪደር ልማት ሥራው ጥራቱን ጠብቆ እየተሠራ ነው” የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ
Next articleየኢትዮጵያ የደን ሽፋን 23 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱ ተገለጸ።