“የኮሪደር ልማት ሥራው ጥራቱን ጠብቆ እየተሠራ ነው” የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ

12

ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች በፒያሳ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ጎበኝተዋል። ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ በጉብኝቱ ወቀት “የኮሪደር ልማት ሥራው ጥራቱን ጠብቆ እየተሠራ ነው” ብለዋል።

የከተማው ሕዝብ ለኮሪደር ልማቱ እያሳየ ያለው ድጋፍ አበረታች መኾኑንም ገልጸዋል። በኮሪደር ልማቱ የተነሱ ነዎሪዎች ለከተማዋ ልማት ያሳዩትን ቁርጠኝነት ያመሰገኑት ከንቲባው በቀጣይ ለሚከናወኑ ልማቶች ኀብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምክንያት አልባው የዋጋ ጭማሪ”
Next article“ሰላማችንን፣ ፍቅር እና መቻቻላችንን ጠብቀን መኖር ትልቅ ጸጋ ነውና እንዳይለየን ጠብቁት” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ