ከ708 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል መሸፈኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለጸ።

15

ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን ከ1ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል በመሸፈን 43 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሠራ ነው። በክልሉ በዘር ለመሸፈን ከታቀደው መሬት ውስጥ እስካሁን ከ708 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ሰብል መሸፈኑን ከቢሮው የተገኘ መረጃ ጠቁሟል።

በምርት ዘመኑ የስንዴ ምርታማነትን በሄክታር ከነበረው 34 ነጥብ 3 ወደ 41 ነጥብ 2 ኩንታል ለማሳደግ እየተሠራ እንደኾነም ነው የተገለጸው። ዕቅዱን ለማሳካት ከዚህ በፊት ከነበረው የግብዓት ሥርጭት በተሻለ ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል ነው የተባለው።

አርሶ አደሮች ሳይንሱ የሚያስቀምጠውን አሠራር እንዲተገብሩ ጥረት እየተደረገ ስለመኾኑም የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡ በክልሉ አሁን ላይ የተሻለ የዝናብ ሥርጭት በመኖሩ በምርት ዘመኑ በሄክታር ለማግኘት የታቀደውን ምርት ማሳካት እንደሚቻል ነው ቢሮው የገለጸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በወር አበባ ዙሪያ በተሠሩ ሥራዎች በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ ቢኾንም ሰፊ ጥረት የሚሹ ጉዳዮች አሉ” ያሉት ዶ/ር መቅደስ ዳባ
Next article“በምክክር ሂደቱ እስካሁን ድረስ ምንም ዓይነት የውጭም ኾነ የውስጥ ጣልቃ ገብነት አልታየም” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ