
ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
የደቡብ ኮሪያ መንግሥት በኢትየጵያ ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የ7 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ደቡብ ኮሪያ ያደረገችው ድጋፍ በዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች አማካይነት የሚሰራጭ መኾኑም ተገልጿል፡፡
ድጋፉ በግጭት ጉዳት ለደረሰባቸው እና ለችግር ተጋላጭ በኾኑ አካባቢዎች ለሚኖሩ የማኀበረሰብ ክፍሎች የሚውል ነው ተብሏል፡፡ እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ደቡብ ኮሪያ በሰብዓዊ እርዳታ ዙሪያ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በቅርበት እና በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መኾኗንም አረጋግጣለች፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!