
ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ እንዳለው የደጀን፣ የመርጦ ለማርያም፣ የሞጣ እና ግንደወይን ከተማ አሥተዳደር ግብር ከፋዮች ናቸው ግብራቸውን አጠናቅቀው የከፈሉት።
ሥራው እንዲሳካ ያልተቋረጠ ድጋፍ እና ክትትል ላደረጉ ለዞኑ መሪዎች፤ ለባለሙያዎች፣ በየደረጃው ለሚገኙ የከተማ አሥተዳደሮቹ መሪዎች፣ ለባለሙያዎች እና ያልተቋረጠ ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ምሥጋና ማቅረቡን ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!