62 ሺህ እናቶች በጤና ተቋማት መውለዳቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ገለጸ።

13

ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዞኑ ጤና መምሪያ ኀላፊ ጌታቸው በለጠ እንዳሉት በ2016 በጀት ዓመት የእናቶችን ጤና ለማሻሻል በቅድመ እና በድኅረ ወሊድ ወቅት ትኩረት ተደርጎ ተሠርቷል።

የነፍሰ ጡር ልየታ እና የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ62 ሺህ በላይ የሚሆኑ እናቶች በጤና ተቋም የወሊድ አገልግሎት አግኝተዋል። ከ584 ሺህ 700 በላይ እናቶች የቤተሰብ ዕቅድ ተጠቃሚ ኾነዋል ብለዋል።

የቤት ውስጥ ወሊድን ለመቀነስ እና የአምቡላንስ ችግሩን ለመፍታት በ92 ጤና ጣቢያዎች የእናቶች ማቆያ በማዘጋጀት ለ15 ሺህ 600 እናቶች አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ነው ኀላፊው የገለጹት።

በዞኑ 12 ጤና ጣቢያዎች የአልትራሳውንድ ምርመራ እንዲጀምሩ ተደርጓል። ሆስፒታሎች ከሚሰጡት አገልግሎት ባለፈ በቀበሌ እና በጤና ኬላዎች ከ16 ሺህ 700 በላይ እናቶች የአልትራሳውንድ ምርመራ እንደ ተደረገላቸው የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

ይሁን እንጅ ከጸጥታ መደፍረስ እና ከአምቡላንስ እጥረት ጋር በተያያዘ አሁንም የእናቶች የቤት ውስጥ ወሊድ መኖሩን ገልጸዋል። በቤታቸው ከወልዱ እና ወደ ጤና ተቋማት ዘግይተው ከመጡ እናቶች ውስጥ ሕይወታቸው ያለፉ መኖራቸውንም ገልጸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጎንደር ከተማ እስራኤል ካሉ እህት ከተሞች ጋር ያላትን ግንኑነት ለማጠናከር ያለመ ምክክር ተካሄደ፡፡
Next article“የአራት ከተማ አሥተዳደር ግብር ከፋዮች ግብራቸውን አጠናቅቀው ከፍለዋል” የምሥራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ