
ባሕር ዳር: ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶመር ባርላቪ ጋር በቱሪዝም፣ የእህትማማች ከተሞችን ለማጠናከር እና የልማት እንቅስቃሴዎችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርጓል። የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ከእስራኤል ምክትል አምባሳደር ጋር በቱሪዝም ዘርፍ፣ በሌሎች የልማት የሥራ እንቅስቃሴዎችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ነው የተገለጸው።
ምክክሩ ጎንደር ከተማ እስራኤል ካሉ እህት ከተሞች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ መኾኑ ተገልጿል። የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሕዝብ ግንኙነት እና አደረጃጀት ዋና አማካሪ ቻላቸው ዳኘው እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አሥተዳደሩ የመሠረተ ልማት ዋና ሥራ አሥኪያጅ አንዱዓለም ሙሉ መሳተፋቸውን ከጎንደር ከተማ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!