
ደሴ: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ የሚገኘው የጎሽ ሜዳ ቧንቧ እና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ከድርጅቱ መሪዎች እና ሠራተኞች ጋር ዓመታዊ የሠራተኞች ቀንን በማክበር፣ የ2016 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ አካሂዷል። በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ጠንካራ ሥራዎች እና በቀጣይ በጀት ዓመት ቢስተካከሉ የተባሉ ሀሳቦች በሪፖርት ተመላክተዋል።
የድርጅቱ ሠራተኞች በበጀት ዓመቱ የተከናወኑት ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡ እንደ ችግር የሚነሱት የመለዋወጫ ችግሮች መፍትሄ ማግኘት ከተቻለ በ2017 ዓ.ም ከዚህ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም ነው ያስረዱት። የጎሽ ሜዳ ቧንቧ እና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት ዋና ሥራ አሥኪያጅ በረደድ ተሰማ “በ2016 በጀት ዓመት 108 ሚልዮን ብር ትርፍ ማስመዝገብ የተቻለበት ስኬታማ ዓመት ነበር” ነው ያሉት።
በመድረኩ በ2016 ዓ.ም ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ለነበራቸው የድርጅቱ ሠራተኞች የዕውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብርም ተካሂዷል።
ዘጋቢ፡- ፊኒክስ ሀየሎም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!