መገናኛ ብዙኃን ለኀብረተሰቡ ወቅታዊ እና የጠራ መረጃ በማድረስ ለሰላም እና ለአብሮነት መጠናከር ቅድሚያ ሰጥተው እንዲሠሩ ተጠየቀ፡፡

15

ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ መገናኛ ብዙኃን ለሀገር ሰላም እና ለሕዝብ አብሮነት መጠናከር ትልቅ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ ተናገረዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ያሉት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባለሙያዎች እና የሥራ ኅላፊዎች የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የለውጥ ሥራዎችን በጎበኙበት እና የልምድ ልውውጥ ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም መገናኛ ብዙኃን ለኀብረተሰቡ ወቅታዊ እና የጠራ መረጃ በማድረስ ለሰላም እና ለአብሮነት መጠናከር ቅድሚያ ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ባለሙያዎች እና የሥራ ኅላፊዎች በበኩላቸው በባለለሥልጣኑ ባደረጉት ጉብኝት መደሰታቸውን ገልጸው የተከናወኑ የለውጥ ሥራዎች ልምድ እና ትምህርት የሚወሰድባቸው እንደኾኑ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ማኀበረሰቡ በተዛባ መረጃ እንዳይታለል ትክክለኛ መረጃን በማድረስ ለሀገር ሰላም እና አብሮነት ቅድሚያ ሰጥተው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለሀገራዊ ምክክሩ ተሳታፊ በተለየባቸው ክልሎች አጀንዳ የመለየት ሥራ እየተከናወነ መኾኑ ተገለጸ።
Next article“108 ሚልዮን ብር ትርፍ ማስመዝገብ የቻልንበት ስኬታማ ዓመት ነበር” የጎሽ ሜዳ ቧንቧ እና ፕላስቲክ ማምረቻ ድርጅት