ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ በሚያደርጉና ምርት በሚከዝኑ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድ መምሪያ አስታወቀ፡፡

9

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሬ በሚያደርጉና ምርት በሚከዝኑ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድ መምሪያ አስታውቋል፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዘውገ ንጉሴ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ያልተገባ አረዳድና ውዥምብር በነጋዴው ማኅበረሰብ እና በሕዝቡ ውስጥ እየተንሰራፋ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተያዘው የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ምክንያት የሚፈጠር የዋጋ ጭማሬን እና የምርት ክዘናን መከላከል ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ ተደርጎ መያዙንም አቶ ዘውገ ነግረውናል፡፡ በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች በግብርና እና በሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ሳይቀር ዋጋ የመጨመርና ምርት የመከዘን አዝማሚያዎች መኖራቸውን በተግባር ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ይህንን ያልተገባ አካሄድ መንግሥት በምንም መልኩ አይታገሰውም ያሉት መምሪያ ኃላፊው ድርጊቱን እየፈጸሙ ባሉ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ እንደተጀመረም ጠቅሰዋል፡ ማኅበረሰቡም በግብይት ወቅት ያለ ምክንያት ዋጋ የሚጨምርና ምርት የሚከዝን ነጋዴ ሲኖር ጥቆማ የማድረስ ኀላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡

በዚህ ተግባር ከተሰማሩ ነጋዴዎች ምርት ባለመግዛትም በአቋራጭ የመክበር አካሄድ የሚመርጡትን መቅጣት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደብረ ብርሃን ዞናል መናኸሪያ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በተደረገው ማሻሻያ የተሻለ አገልግሎት እያገኙ እንደኾነ ተገልጋዮች ተናገሩ።
Next articleየአውሮፕላን ቲኬት ዋጋን በተመለከተ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ ማብራሪያ።