የነሐሴ 2016 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለጸ።

24

ባሕር ዳር: ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የነሐሴ 2016 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ምንም ጭማሪ ሳይደረግበት ሐምሌ ወር ላይ በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑ ተገልጿል። በመኾኑም የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት ወንጀል በመራቅ እና የዋጋ ጭማሪ ባለማድረግ የመንግሥትን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት በየደረጃው የሚገኙ የንግድ መዋቅሮች በነዳጅ ስርጭት እና ሽያጭ ዙሪያ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ሥራዎች ተጀምረዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል ከአምራች ኢንዱስትሪዎች ከ134 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።
Next articleበደብረ ብርሃን ከተማ ሰላምን በዘላቂነት ለማስጠበቅ ነዋሪውን ያሳተፈ ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚገባ ተገለጸ፡፡