“የፓርቲ መዋቅርን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር መምራት የሞት ሽረት ጉዳይ ነው” በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ

40

ባሕር ዳር: ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የ2016 በጀት ዓመት የተግባራት አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ ላይ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ፍስሃ ደሳለኝ እና ሌሎችም የክልል፣ የዞንና የከተማ አሥተዳደር የፖርቲ አመራሮች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ “ከላይ እስከ ታች የሚገኙ የፖርቲ መዋቅሮችን በማጠናከር ተግባራትን በመናበብ፣ በቅንጅት እና በማስተሳሰር በውጤታማነት መምራት የሞት ሽረት ጉዳይ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። የፓርቲው መዋቅር ሚናው ከፍ ያለ ነው ያሉት ኀላፊው፣ መዋቅሩ እንደ አስኳል ኹኖ ሁሉንም ተግባራት የመምራት እና የማስተሳሰር ኀላፊነትን በማጠናከር የፖለቲካ ሥራዎችን በላቀ ትኩረት መሥራት ይገባልም ብለዋል። በሁሉም ተግባራት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብም በሁሉም እርከኖች ግልጽ ውይይት እና መግባባት እንደሚጠይቅ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በድረ ገጹ ባስነበበው መረጃ ገልጿል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እንደ መሪ በየደረጃው ያለን አመራሮች በክልላችን ጉዳይ ኀላፊነት መውሰድ አለብን” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleከ1ሺህ 500 በላይ ሕገ ወጥ ተዘዋዋሪዎች ወደ መጡበት መመለሳቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አስታወቀ።