“ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል” የኮሌጁ ዲን ተስፋሁን መኮንን

43

ባሕር ዳር: ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኮሌጁ ከደረጃ አንድ እስከ ደረጃ አምስት ያሠለጠናቸውን 8 መቶ 22 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል። በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን ተስፋሁን መኮንን ተመራቂዎቹ ባለፋት ዓመታት በአስር የሥልጠና ዘርፎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ምዘናውን ያለፉ ናቸው ብለዋል።

“ጎንደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ለኢንዱስትሪው ዘርፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል” አቶ ተስፋሁን። ከ8 መቶ 22 ተመራቂዎች 6 መቶ 33ቱ የሥራ ዕድል ሥልጠና ማግኘታቸውንም ገልጸዋል።

ተመራቂ ተማሪዎችም ከኮሌጁ ያገኙት እውቀት እና ክህሎት በቀጣይ በሥራ ለመሠማራት እንደሚያግዛቸውም ነው የተናገሩት። ለተመራቂ ተማሪዎች የሥራ መመሪያ ያስተላለፉት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ተወካይ ሁንዓለም አሻግሬ ተመራቂዎች የነገ ኢትዮጵያን ለመገንባት ትልቅ ሙያዊ ኅላፊነት አለባችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ተስፋዬ አይጠገብ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ በተቀናጀ መልኩ ተጠናክሮ ይቀጥላል” ካሳሁን ጎፌ (ዶ.ር)
Next article“የታቀዱ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች እንዲሳኩ የአሥተዳደር ጉዳዮች ክላስተር ጠንክሮ ይሠራል” አቶ ደሳለኝ ጣሰው