ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

41

ባሕር ዳር: ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡና ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የገንዘብ ድጋፋን የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈቲህ ማህዲ (ዶ.ር) እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ስለሺ ኮሬ (ዶ.ር) በጎፋ ዞን አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት በመገኘት አስረክበዋል። በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ምክር ቤቱና አባላቱ ማዘናቸው እና የሚያደርጉት ድጋፍም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በወቅቱ ተገልጿል።

ምክር ቤቱ ካደረገው የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ የምክር ቤቱ አባላት፣ የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች 340 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተጠቅሷል። የቡድኑ አባላት አደጋው በደረሰበት ቦታ በአካል በመገኘት የአደጋውን ተጎጂዎችና የተጎጂ ቤተሰቦችን ማፅናናታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ የምክር ቤቱ የልዑካን ቡድን አባላት በአካል በመገኘት ላደረጉት ድጋፍ አና ላሳዩት ወገንተኝነት አመሥግነዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሥልጣኔ ቀንዲል!
Next articleብዝኃነታችንን የያዝንበት መንገድ…