
ባሕር ዳር: ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በሚገኘው ታዋቂ የባሕር ዳርቻ ላይ በደረሰው አሰቃቂ የሽብር ጥቃት በሰው ሕይወት መጥፋት እና በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ሀሳባችን በጥቃቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ወገኖች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ከሶማሊያ ሕዝብ ጋር ነው ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!