የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው።

52

ባሕር ዳር: ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት አስተባባሪ ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ.ር)ን ጨምሮ የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በመርሐ-ግብሩ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት ሱፐርቪዥን ሪፓርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝ ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት በበጀት ዓመቱ የተገኙ መልካም ልምዶችን አቅም አድርጎ ለማስቀጠልና የተስተዋሉ ክፍተቶችን ደግሞ በቀጣይ ለማስተካከል በዝርዝር እንደሚገመገምም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከግማሽ በላይ የሚኾኑት ተመራቂዎች ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የመጡ ናቸው” የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዘመነ ሀብቱ
Next article“ለጊዜ እና ለዓላማ ልዩ ትኩረት መስጠት ይገባል” ተመራቂ ተማሪዎች