
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 26/2012 ዓ.ም (አብመድ) የጣና ሐይቅ ኮሌጅ አዴት ‘ካምፓስ’ ከ100 በላይ ታካሚዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሦስት ሕንጻዎችን ለይልማና ዴንሳና ጎንጂ ቆለላ ወረዳዎችና ለአዴት ከተማ አስተዳደር እንዲሰጥ ቦርዱ መወሰኑን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡
ኮሌጁ ከከተማ ወጣ ያለ መሆኑ ለለይቶ የሕክምና ክትትል ማድረጊያ ቢውል ለኅብረተሰቡ ሥጋት እንደማይሆንም በደብዳቤው አመላክቷል፡፡
የእንጅባራ ጤና ሳይንስ እና ቢዝነስ ኮሌጅ ደግሞ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት እንደዘገበው ኮሌጁ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የኮሮና ወረርሽኝ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል 10 ሺህ ብር እና ለእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ደግሞ 15 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ የኮሌጁ ሥራ አስኪያጅ አያና ስማቸው (ዶክተር) ከሙያ ድጋፍ ባለፈ ማኅበረሰቡን በገንዘብ በማገዛቸው ደስተኛ እንደሆኑም ተናግረዋል፡፡