
ባሕር ዳር: ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
አንጋፋው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች ቁጥር 8 ሺህ 524 መኾናቸውን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር) ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ መምህራን፣ ተመራቂ ተማሪዎች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና የተመራቂ ወላጆች ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!