አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ በሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛን ተቀብለው አነጋገሩ።

88

ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ በሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሪሎ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ዛሬ ተወያይተዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ በኾኑ ጉዳዮች እና በተለይም በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሱዳን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ (ዶ.ር) በማድረግ ላይ ስለሚገኙት ጥረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ ለልዩ መልዕክተኛው ገልጸዋል።

በወቅቱ በሱዳን ሰላም እና ፀጥታን በዘላቂነት ለማስፈን በጋራ ለመሥራት ሁለቱ ወገኖች ተስማምተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በመሥራት ውጤት ተመዝግቧል” የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት
Next articleባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።