“የቦሌ መንገድ የመዲናችን አዲስ አበባ የደመቀ የንግድ እና የዘመናዊ እንቅስቃሴ አገልግሎቶች ማዕከል ነው።”የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

16

ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ወደ ቦሌ ዓለምአቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ እና ወደሌሎች የከተማዋ ክፍሎች ለሚደረግ ጉዞ ለተቀላጠፈ የትራንስፖርት ግልጋሎት የሚውል መስመርም ነው ብሏል ጽሕፈት ቤቱ። በመንገዱ የሚገኙ የተለያዩ የቢዝነስ ማዕከላት፣ ሆቴሎች፣ሬስቶራንቶች እና ሱቆች የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጎብኝዎችን ቀልብ የሚስቡ መኾናቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ገልጿል።

ለባለፉት ጥቂት ወራት የቦሌ መንገድ በኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ የአዲስ አበባን የኢኮኖሚ እድገት እና የከተማ ልማት ጥራት በሚያሳይ ሁኔታ ከፍ ያለ ሥራ ሲሠራ እንደነበርም ነው የተገለጸው።

ከቦሌ ድልድይ እስከ መስቀል አደባባይ የተሠራው ሥራ ሌሎች ተግባራትን ጨምሮ የሚከተሉትን ዐበይት ክንውኖች ያካተተ ነው:-

👉 የ4.3 ኪሎ ሜትር የመንገድ ልማት
👉 የ10 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ ግንባታ
👉 የ13.2 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ ግንባታ
👉 የ30,160 ካሬ ሜትር የግራናይት እና ባሳልት ንጥፍ ሥራ
👉የ30 የአውቶቡስ እና ታክሲ መቆሚያ ሥራ
👉 የ10 የመኪና ፓርኪንግ ስፍራዎች ሥራ
👉 ከ10 በላይ የሆኑ አነስተኛ የሕዝብ ፓርኮች እና ማረፊያ ፕላዛዎች
👉 ከ500 በላይ የሚሆኑ የመንገድ ዳር ሕንፃዎች እና ቤቶች ጥገና እና እድሳት

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የኢትዮጵያ ባንኮች ህልውናን ያስቀጠለ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“ዕቅድ ብቻውን ዋጋ የለውም፣ ለዕቅድ አፈጻጸም ሥነ ምግባር ያስፈልጋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ