በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ በሳጋ ወንዝ ላይ የተገነባው ተንጠልጣይ ድልድይ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።

15

ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ በሳጋ ወንዝ ላይ የተገነባው 100 ሜትር ተንጠልጣይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል። የክልሉ መንግሥት በመሠረተ ልማት ተደራሽ ያልኾኑ አካባቢዎችን ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እየሠራ ነው ተብሏል።

80 በመቶ በክልሉ መንግሥት እና 20 በመቶ ሄልቬታስ ኢትዮጵያ መቀናጆ በጀት ድጋፍ በክልሉ ሁሉም ዞኖች ተንጠልጣይ ድልድዬች ተገንበተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። በክልሉ መንገድ ቢሮ ባለቤትነት በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ በሳጋ ወንዝ ላይ የተገነባው100 ሜትር ተንጠልጣይ ድልድይ ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።

የድልድዩ መገንበት የአካባቢውን ማኅበረሰብ የዘመናት ጥያቄ የመለሰ ነው ያሉት የአካባቢው ነዋሪዎች በክረምት ወቅት በሰው፣ እንስሳት እና ንብረት ላይ ይደርስ የነበረው ጉዳት መፈታቱን ገልጸዋል። ከክልሉ መንገድ ቢሮ እንዳገኘነው መረጃ በተንጠልጣይ ድልድዩ መገንባት እና የክልሉ መንግሥት የሕዝብን ችግር አዳምጦ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠቱ ምስጋና አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኀብረተሰቡ ከጎርፍ እና ከመሬት መንሸራተት አደጋ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ።
Next articleየእናቶች ፈተና!