በደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

18

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ድጋፉ የተደረገው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ማስተባበሪያ ነዉ።

በኮሚሽኑ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የንጽህና አጠባበቅ ባለሙያ አቶ ናታኒየም ሀይሉ እንደተናገሩት የተደረገዉ ድጋፍ የንጽህና መጠበቂያ ቁሶች ናቸው፡፡ ይህም በክረምት ወቅት ከንፅህና ጉድለት ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

አቶ ናታኒየም ሀይሉ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ በጤናው ዘርፍ በተለይም ተፈናቃዮች የተኝቶ ሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

በደብረብርሃን ከተማ ጤና መምሪያ የንጽህና እና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ቡድን አስተባባሪ አቶ በየነ ሳህሉ የተደረገዉ ድጋፍ በክረምት ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ በሽታዎችን ለመከላከል ያግዛል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማት ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ማስተባበሪያ ያደረገዉ ድጋፍ ለ800 አባዎራዎች ተደራሽ ይኾናል ተብሏል።

ዘጋቢ፦ ገንዘብ ታደሰ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በኢንዱስትሪ ፓርኮች የቻይና ባለሀብቶችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየሠራን ነው” ዶክተር ፍሰሃ ይታገሱ
Next articleደም በመለገስ የወላድ እናቶችን ሞት መቀነስ እንደሚገባ የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡