
አካኼዳችን ድኻ ተኮር ነው። ትኩረታችን ለችግር በመጠቃት ተጋላጭ የሆኑ ደካሞችን መደገፍ ነው። የለውጥ ሥራዎቻችን ሁሉ ስኬት በባለድርሻ አካላት የተባበረ ጥረት ላይ ይመሠረታል። ይህም ምርታማነትን፣የውጭ ንግድን እና ገቢን ተባብሮ ማሳደግ ማለት ነው። የሕግ አስፈጻሚ አካላት የለውጥ ሥራውን ባልተገባ ሕገ ወጥ መንገድ ለመጠቀም በሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ ርምጃ እብዲወስዱ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል።
ከላይ የጠቀስኳቸውን ሐሳቦች ዛሬ ጠዋት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በነበረኝ መድረክ ገልጫለሁ። የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የመድረኩን ውይይት በሚዲያዎች መከታተል ይቻላል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)