
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ “ባሕር ዳር ውብ ብቻ አይደለችም፤ ውበት ናት!” በሚል ገልጸዋታል። ዛሬ በከተማዋ የሚገኘውን የባህር ዳር ስታዲየም ያለበትን ደረጃ ተመልክተናል ብለዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ስታዲየሙ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማስተናገድ እንዲችል ተድረጎ እየተገነባ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡
በግንባታ ምዕራፍ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ስታዲየሙ በቀጣይ ዓመት ግንባታው ተጠናቅቆ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንዲችል ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
አቶ ተመስገን በቆይታችንም በባሕር ዳር ስታዲየም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አካሂደናል ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።
በባሕርዳር ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ልባዊ አቀባበል ላደረጉልን የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች ብሎም ለከተማዋ ከንቲባ እና ሕዝብ ላቅ ያለ ምሥጋና አቀርባለሁ ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!