
ባሕር ዳር: ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በሦስተኛ ቀን ውሎው የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ተጠናቅቋል። ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ያቀረቡትን ሹመት የምክር ቤቱ አባላት መርምረው አጽድቀዋል።
በዚህም፦
1. አቶ ዓለምአንተ አግደው ወንድሜነህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት
2. ሙሉዓለም ቢያዝን ዓለሙ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት
3. አቶ መልካሙ ፀጋየ ገላው የባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ ኾነው ተሹመዋል።
በተጨማሪም በክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ የቀረቡ የቋሚ ኮሚቴ አባላት ለምክር ቤቱ ቀርቦ ጸድቋል።
1. የሰው ሃብት አሥተዳደር እና ቱሪዝም ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ አበራ ፋንታው
2. የመንግሥት ወጪ ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ እመቤት ከበደ ኾነው ተሹመዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!