
ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎ እንደቀጠለ ነው፡፡
በምክር ቤቱ የሦስተኛ ቀን ከሰዓት በኋላ ውሎ የክልሉን መንግሥት የ2017 በጀት ተወያይቶ አጽድቋል፡፡
የክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት 150 ቢሊየን 666 ሚሊየን 531 ሺህ 527 ብር እንዲኾን የቀረበለትን በጀት ተወያይቶ በመሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!