የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ሥምምነት አጸደቀ።

31

አዲስ አበባ: ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸካይ ስብሰባ ዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ጋር የተደረገውን የፋይናንስ ድጋፍ ሥምምነት ለማጽደቅ በተዘጋጀው አዋጅ ላይ ተወያይቶ አጽድቋል።

የፋይናንስ ድጋፍ ሥምምነቱ የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያስገኝ ነው። ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የእርዳታና 500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ደግሞ በብድር መልክ የተገኘ ነው ተብሏል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ የብድር ስምምነቱ ኢትዮጵያ ተግበራዊ ለምታደርገዉ ሀገር በቀል ሪፎርም አጋዥ መኾኑን ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ኤልሳ ጉዑሽ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየተማሪዎች ምዝገባ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወነ ነው” የምሥራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ
Next articleምክር ቤቱ የተለያዩ አዋጅ እና ደንብን መርምሮ አጸደቀ፡፡