የአማራ ክልል ምክር ቤት የሥነ ምግባር ግድፈት የታየባቸውን አራት የወረዳ ዳኞችን አሰናበተ፡፡

129

ባሕር ዳር: ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎ ተጀምሯል፡፡ ምክር ቤቱ በሦስተኛ ቀን ረፋድ ቆይታው ተጠሪነታቸው ለምክር ቤቱ የኾኑ ተቋማትን የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ያዳምጣል፡፡

ምክር ቤቱ በትናንትናው የከሰዓት በኋላ ውሎው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዕቅድን እና የምክር ቤቱን የሕግ፣ ፍትሕ እና አሥተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የውሳኔ ሃሳብን አድምጦ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡ በመጨረሻም ምክር ቤቱ በሥራቸው ላይ የሥነ ምግባር ግድፈት የተስተዋለባቸውን አራት ዳኞች ከሥራ አሰናብቷል፡፡ ዳኞቹ ከዳኝነት ሙያ ጋር የተያያዘ የሦስት ዓመት እግድም ተላልፎባቸዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article38ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች
Next article“በፓርኩ ወጣቶችን በማደራጀት የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል” የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ