390 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

19

ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን 390 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ዛሬ ወደ ሀገር የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲኾኑ ከተመላሾች መካከል 10 ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያ እና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ70 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

በተመሳሳይ በትናንትናው ዕለት ከየመን 143 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሰዎች ዝውውው መከላከል እና የተመላሽ ዜጎች ክትትልና ድጋፍ መሪ ሥራ አሥፈጻሚ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleተላላፊ ያልኾኑ በሽታዎችን መከታተል እና መቆጣጠር እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
Next articleየብሪክስ ወጣቶች ጉባዔ የአባል ሀገራቱ ወጣቶች በጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ እንዲመክሩ እድል እንደፈጠረ ተገለጸ።