
ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የጸሐፊን መንፈስ የሚያድሱ ሐይቆች፣ ተፈጥሮን አድምጦ ጥዑም ዜማ ለመቀመር የሚያስችል ድንቅ መልክዓ ምድር፣ የተፈጥሮን ስክነት ማሳያ ስፍራ በሚል ገልጸዋታል የውኃዋ ከተማን ቢሾፍቱ።
የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ መልእክት የጀመርነውን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በቢሾፍቱም ቀጥለናል ነው ያሉት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት፡፡
በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ተነሳሽነቶችን በማስተዋወቅ ለመጪው ትውልድ አረንጓዴ ተፈጥሮና ጤናማ ምድርን እናስረክባለን ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!