
ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተ-መንግሥት እድሳት ስለመጀመሩ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እድሳቱን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት እድሳቱ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይም ይገኛል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ “የፋሲል ቤተ-መንግሥትን ወደ ቀደመ ግርማ ሞገሱ እንመልሰዋለን” ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!