የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ ተጀምሯል፡፡

69

ባሕር ዳር: ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ ተጀምሯል፡፡ በምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የክልሉን መንግሥት ዓመታዊ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በምክር ቤቱ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ እየቀረበ ነው፡፡ የክልሉን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር እቅድ ለምክር ቤቱ የሚያቀርቡት የአማራ ክልል ፕላን እና ልማት ቢሮ ኅላፊ ደመቀ ቦሩ (ዶ.ር) ናቸው፡፡

የክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት የልማት እና መልካም አሥተዳደር እቅድ ከቀረበ በኋላ በምክር ቤት አባላቱ ውይይት ተደርጎበት ይጸድቃል ተብሎ ይታሰባል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ በከፍተኛ መስመር ላይ ባጋጠመ ጉዳት በተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል ተቋርጧል።
Next article“የፋሲል ቤተ መንግሥትን ወደ ቀደመ ግርማ ሞገሱ እንመልሰዋለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)