የከፍተኛ ትምህርት፣ የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ እንዲሁም የፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያ ወጣ፡፡

27

ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት እና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ፈቃድ እና የፈቃድ ዕድሳት አሰጣጥ መመሪያን አውጥቷል። ሚኒስቴሩ አዲስ ባወጣው መመሪያ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ አሰጣጥ እና ዕድሳትን በተመለከተ ያለውን አሠራር ለማሻሻል እና ለማዘመን ብሎም በዘርፋ የሚታዩ የሕጋዊነት ችግሮችን ለመቅረፍ በማሰብ መመሪያው መውጣቱን በትምህርት እና ሥልጠና ባለሥልጣን የከፍተኛ ትምህርት ፍቃድ አሰጣጥ መሪ ሥራ አሥፈጻሚ ሕይወት አሰፋ ገልጸዋል።

አዲስ በተዘጋጀው መመሪያ መሠረት በአዲስ የሚቋቋሙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት ፦
👉የመመስረቻ ጹሑፍ
👉የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ
👉የንግድ ምዝገባ እና የንግድ ሥራ ወይም የኢንቨስትመንት ፈቃድ የያዙ ሕጋዊ ሰነዶችን ማሟላት አለባቸው ተብሏል።
ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፡-
👉 ራሱን የቻለ አደረጃጀት
👉የግብዓት እና የመማሪያ ሕንፃ እና
👉ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው ሲል መመሪያው አስቀምጧል።

መመሪያው መዘጋጀቱ ተቋማት የትምሀርት እና ሥልጠና መስኮቻቸውን በአዲሱ የፈቃድ አሰጣጥ ስታንዳርድ መሠረት ለመገምገም እና ለመመዝገብ ያገለግላል ነው ያሉት። በፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓቱ አልፈው ያልተመዘገቡ ተቋማትንም በመገምገም እንደ ሀገር ወጥነት ያለው የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግም ይረዳል ብለዋል።

በመንግሥት እና በግል ተቋማት መካከል ያለውን የፈቃድ አሰጣጥ የአሠራር ሥርዓት ልዩነትን ለማስቀረትም እንደሚረዳ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኅብረተሰቡ ከጎርፍ እና ውኃ ሙሌት አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ መንግሥት አሣሠበ።
Next article“አሁን የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ለማጽናት እና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያስችሉ አማራጮችን ሁሉ ማየት ይገባል” የምክር ቤት አባላት