
ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2016 በጀት ዓመት 7 ነጥብ 02 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የግሩፑ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ መስፍን ጣሰው በሰጡት መግለጫ አየር መንገዱ የዓለም አቀፍ መዳረሻውን ወደ 139 ማሳደጉን ተናግረዋል፡፡
የሀገር ውስጥ በረራ መዳረሻውም 22 መድረሱን ነው የገለጹት፡፡
ፈጣን፣ ተመራጭ እና አስተማማኝነቱን እያረጋገጠ የመጣው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዕድገት ጉዞው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ የያቤሎ፣ ሚዛን አማን፣ ጎሬ መቱ፣ ነጌሌ ቦረና እና ደብረ ማርቆስ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በቀጣይ ዓመት አጋማሽ ጀምሮ አንደሚጠናቀቁ ተመላክቷል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!