
ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ፍሰሀ ይታገሱ (ዶ.ር) በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያለው የኢኮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እሳቤ አበረታች መኾኑን ገልጸዋል። ዋና ሥራ አሥፈፃሚው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የሥራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው ተመልክተዋል።
በምልከታቸውም በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎችን በመጎብኘት ከሀገር በቀል እና ከውጪ ኢንቨስተሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም አምራች ኩባንያዎች ስላሉበት የምርት እንቅስቃሴ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የኤክስፖርት እና የተኪ ምርት ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እና አፈፃፀሞች ላይም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ኢንዱስትሪ ፓርኩ ለኢንቨስተሮች ያለው ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታ እና በፓርኩ ለኢኮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት የተሠሩ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች እንደ ሀገር የሚከናወነውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በእጅጉ የሚያግዙ መኾናቸውም በዕለቱ ተገልጿል። በኢንዱስትሪ ፓርኩ ከነበረው ፕሮግራም ጎን ለጎን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስለመከናወኑ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!