
ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) አሜሪካ የበለጠ ነፃ እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በኢትዮጵያ መንግሥት የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲኾን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር እንደምትደግፍ አረጋገጠች፡፡
ገበያ መር የውጭ ምንዛሪ አካሄድ ከባድ ቢኾንም የተዛባውን የሀገሪቱን ማክሮ ኢኮኖሚ ለመጠገን ወሳኝ እርምጃ መኾኑን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳስታወቀው አሜሪካ የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲኾን ከልማት አጋሮች ጋር በመኾን ድጋፍ ታደርጋለች፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!