የአማራ ክልል ምክር ቤት ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል፡፡

53

ባሕር ዳር: ሐምሌ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከደቂቃዎች በኋላ ይጀምራል፡፡

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቆየው የምክር ቤቱ ጉባኤ የ2016 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርትን አድምጦ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የ2017 በጀት ዓመት የክልሉ መንግሥት ዕቅድን መርምሮ ያጸድቃል፡፡

ምክር ቤቱ በመጨረሻም የ2017 በጀትን መርምሮ ያጸድቃል፡፡ አሚኮ የምክር ቤቱን ውሎ በሁሉም ሚዲየሞቹ እየተከታተለ ያቀርባል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያውን የተሳካ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማከናወኑን አስታወቀ።
Next article“በክልሉ የተፈጠረውን የሰልም እጦት በዘላቂነት ለመፍታት ውይይት እና ድርድር ምርጫ ሳይኾን ብቸኛ አማራጭ ነው” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋየ