ምሥጋና 🙏

13

ዛሬ የምናመሠግነው የአትሌቲክስ ጀግናውን አበበ ቢቂላን ነው።
🙏 በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በደብረ ብርሃን አውራጃ ልዩ ስሟ ጃቶ በምትባል ሥፍራ ነሐሴ 30/1925 ዓ.ም ተወለደ
🙏 በታዳጊነቱ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት በክብር ዘበኛ በወታደርነት ተቀጠረ።
🙏 በ24 ዓመቱ አትሌቲክስን ጀመረ
🙏 ለመጀመሪያ ጊዜ በሮም ኦሎምፒክ ተሳትፎ አሸነፈ፡፡ ከዚያም በ1953 ዓ.ም በተካሄደው የአቴንስ ማራቶን በድጋሚ በባዶ እግሩ በመሮጥ አሸናፊ ኾኗል፡፡ ይህ ውድድር የመጨረሻው በባዶ እግሩ የሮጠበት ውድድር ነው
🙏 ከሁለት ዓመታት በኋላ በ1955 ዓ.ም በቦስተን ማራቶን ተወዳድሮ 5ኛ የወጣ ሲኾን ከተወዳደረባቸው ዓለም አቀፍ ውድድሮች ያላሸነፈበት ብቸኛው ውድድር ነው
🙏 ባጋጠመው የትርፍ አንጀት ሕመም ምክንያት ቀዶ ጥገና አድርጎ ስለነበር በቶኪዮ የ1956 ዓ.ም ኦሎምፒክ ይሳተፋል ተብሎ አልታሰበም ነበር። ነገር ግን ውድድሩን 2:12:11.2 በኾነ ሰዓት በማጠናቀቅ የራሱን የሮም ኦሎምፒክ ማራቶን ክብረ ወሰን አሻሽሎ ውድድሩን በአንደኝነት አጠናቋል
🙏 ድሉ በሁለት ተከታታይ የኦሎምፒክ ማራቶን ውድድር ላይ ወርቅ ያገኘ የመጀመሪያው አፍሪካዊ አድርጎታል
ከተወዳደረባቸው 15 የማራቶን ውድድሮች 13ቱን ያሸነፈ ሲኾን አንዱን በጉዳት ምክንያት ሲያቋርጥ በሌላኛው ውድድር ደግሞ 5ኛ ወጥቷል
🙏 በ1961 ዓ.ም በደረሰበት የመኪና አደጋ ከእጆቹ በቀር ሰውነቱን ማንቀሳቀስ ተቸገረ፡፡
🙏 በቀስት ውድድር እና በሌሎች ዘርፍ በአካል ጉዳተኞች ኦሎምፒክ ተሳትፎ አሸናፊ ኾኗል፡፡
🙏 በ41 ዓመቱ ጥቅምት 15/1966 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
🙏 የአትሌቲክሱ ጀግና አበበ ቢቂላ ስሙ በወርቅ የተጻፈ የምንጊዜም የዓለም ባለልዩ የድል ሆኖ ስሙ ሲጠራ ይኖራል። ጀግናው አቤ በሮም እና በአዲስ አበባ ዝናውን እና ክብሩን የሚመጥኑ ማስታወሻዎች የተቀመጡለት ወደር የማይገኝለት የስኬት ሰው ሆኖ እየታወሰ ይኖራል።

Previous article#ሳምንቱ በታሪክ
Next articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ስርዓት ማሻሻያ አደረገ።