የሃዘን መግለጫ!

75

ባሕር ዳር: ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከሰሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጓዙ በደረሰ አደጋ ሕይዎታቸው ባጡ ወገኖች የተሰማውን ሃዘንገልጿል።

የክልሉ መንግሥት በመግለጫው በ20/11/2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ገዳማ በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከሰሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጎዙ ከነበሩት 26 ሰዎች መካከል የ12 ሰዎች ሕይዎት አልፏል።

የአማራ ክልል መንግሥት በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አደጋ የተሠማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ሕይዎታቸውን ላጡ ቤተሠቦች እና ወዳጅ ዘመዶች መጽናናትን ይመኛል ብሏል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ባሕር ዳር

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ጸጥታ ምክር ቤት የተለያዩ የክልከላ ውሳኔዎችን ማሳለፋን አስታወቀ።
Next articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻያን አስመልክቶ የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፦