“በበጀት ዓመቱ ከ512 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ችለናል” የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ

35

ባሕር ዳር: ሐምሌ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት 529 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ512 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ተናገሩ፡፡

ከአምናው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ገቢው ከ70 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለውም ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለውም ዘመናዊ እና ተደራሽ የታክስና የጉምሩክ አሥተዳደር ሥርዓትን በመገንባት አዳዲስ አሠራሮችን በመቅረፅ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ ገቢ አሰባሰቡን ውጤታማ በማድረግ የዕቅዱን ከ96 በመቶ በላይ እንዲሳካ አስችሏል ብለዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ሕገወጥ ንግድ እና ኮንትሮባንድ በሀገራዊ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱ ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንዳሳረፈም ነው የገለጹት።

በቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሕጋዊነትን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ትብብር እንዲያደጉ ሚኒስትሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የተጠናቀቀውን እና አዲሱን በጀት ዓመት አስመልክቶ ያዘጋጁት የጋራ የውይይት መድረክ ዛሬ በአርባምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መሪዎች ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የመከላከያ መሪዎች ጋር ተወያዩ።
Next articleበአማራ ክልል 5 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በኮሌራ በሽታ መያዛቸውን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።