ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

37

ባሕር ዳር: ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 051 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በሦስት ዙር በተከናወነ በረራ ወደ ሀገር የተመለሱት 1001 ወንዶች፣ 44 ሴቶች እና 6 ጨቅላ ህፃናት ናቸው፤ ከእነዚህም መካከል 37 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የኾኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ69 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጥራት ያላቸው የጤና መረጃዎችን በመሠብሠብ ለሀገሪቱ የፖሊሲ ግብዓት ማዋል የሚያስችል ሥልጠና ተሰጠ፡፡
Next articleየባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡