
እንጅባራ: ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአራተኛ ዙር የግንባታ ምእራፍ የተገነቡት ፕሮጀክቶቹ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቁ ናቸውም ተብሏል።
ግንባታቸው ተጠናቅቀው ለምረቃ ከበቁት መሠረተ ልማቶች መካከል ዘመናዊ የአሥተዳደር ሕንፃዎች፣ የተማሪዎች ማደሪያና መማሪያ ሕንፃዎች ይገኙበታል፡፡
የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማዘመን የተገዙ ማሽነሪዎችም የፕሮጀክቱ አካል ናቸው ተብሏል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር) አሁን ላይ ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለምረቃ የበቁት መሠረተ ልማቶች የዩኒቨርሲቲውን ተመራጭነት የሚጨምሩና የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ ለበለጠ ሥራ የሚያነሳሱ ናቸው ብለዋል።
የእንጅባራ ከተማና አካባቢው ማኅበረሰብ ለዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ ስኬታማነት የሚያደርገው ድጋፍ የሚደነቅ እንደኾነም ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው በግብርና፣ በጤና እና ቱሪዝም የትኩረት መስኮች የአካባቢውን ማኅበረሰብ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ስለመኾኑም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።
በምረቃና በጉብኝት መርሐ ግብሩ የተገኙት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ዩኒቨርሲቲው የለያቸው የትኩረት መስኮች ለአካባቢው ማኅበረሰብ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው መኾናቸውን ተናግረዋል።
የሀገራችን ችግሮች በዘላቂነት የሚፈቱት ብቁ የሰው ኃይል ማፍራት ሲቻል መኾኑን ያነሱት ዋና አሥተዳዳሪው በትምህርት ጥራት ላይ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አስገንዝበዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የተጋበዙ የአካባቢው ነዋሪዎችም ዩኒቨርሲቲው የጀመራቸው የምርምር፣ የመማር ማስተማርና በማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀዋል።
በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያም ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በሚኾን ወጪ የሚገነባው የዩኒቨርሲቲው የባሕልና የስብሰባ አዳራሽ፣ የአገው ባሕልና ቋንቋ ጥናት ኢንስቲትዩት ማዕከል ግምባታ መሠረት ድንጋይ ተቀምጧል።
ዘጋቢ፡- ሳሙኤል አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!