
ባሕር ዳር: ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እስካሁን የ231 ዜጎችን ሕይዎት እንደቀጠፈ በተረጋገጠው የጎፋ ዞን የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ቤተሰቦች እና ማኅበረሰብ በአካል ለማፅናናት በስፍራው ተገኝተዋል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እና ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከቀድሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ እንዲሁም ከሌሎች ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ጋር በስፍራው ሲገኙ በክልል ኀላፊዎች እና በማኀበረሰቡ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!